"ታላቅ የህዝብ አደራ ስላለብን ለቀጣይ ተልእኮ ራሳችንን መዘጋጀት አለብን "ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች በ2013 በጀት ዓመት ዕ...

"ታላቅ የህዝብ አደራ ስላለብን ለቀጣይ ተልእኮ ራሳችንን መዘጋጀት አለብን "ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች በ2013 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም እና የ2014 መሪ ዕቅድ ላይ መወያየት ጀምረዋል፡፡ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በውይይቱ መክፈቻ እንደተናገሩት ተግዳሮቶችን በማለፍ የኢትዮጵያን ብልፅግና ለማረጋገጥ ወሳኝ ወቅት ላይ በመሆናችን የተናበበና የተጠናከረ አመራር ለመስጠት ወቅታዊ ሁኔታውን በሚገባ መረዳት እንደሚገባ አስረድተዋል። የ2013 ዓ.ም ዕቅድ ለውጡን መነሻ በማድረግ በ2011 እና በ2012 የነበሩ ድሎችን በማጉላትና ጉድለቶችን በማረም ለውጡን ለማስቀጠል ባደረግነው ጥረት የተመዘገቡ ድሎችንና የነበሩ ክፍተቶችን እንፈትሻለን ብለዋል። ስድስተኛው አገራዊ ምርጫ ሰላማዊና ዴሞክራሲያዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የነበሩ አበረታች ስራዎችን በመዳሰስ ክፍተቶቻችንን አርመን ሀገራዊ ለውጡን ለማስቀጠል እና ህዝቡ በድምፁ የሰጠንን ሀላፊነት በአግባቡ ለመወጣት የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች የሚቀመጡበት መድረክ እንደሚሆንም ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ አብራርተዋል። በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማዕከል አስተባባሪ አቶ መለሰ አለሙ በበኩላቸው አመራሩ በዓመቱ መጀመሪያ ላይ ለውጡ በድል፣ በስኬትና በተግዳሮት የታጀበ መሆኑን ገልጸዋል ። በዚህም ወደ ተግባር በመገባቱ ሀገራዊ ምርጫው በሰላም ማጠናቀቅ፣ የኮቪድ 19 ወረርሽን ተፅዕኖ ለመቀነስ መረባረብ፣ 2ኛውን የህዳሴ ግድብ ሙሌት እና የመሳሰሉ ሀገራዊና ከተማዊ ጉዳዮችን በስኬት ማጠናቀቅ መቻሉን አስረድተዋል። ዛሬ በጀመረው የውይይት መድረክ አመራሩ የነበሩትን ጥንካሬዎች አንጥሮ በማውጣት እንዲሁም ጉድለቶችን በመፈተሽ ለግብአትነት በመጠቀም በቀጣይ ሀገራዊ ለውጡን አጠናክሮ ለማስቀጠል የጋራ መግባባት እንደሚያዝበትም አቶ መለሰ ገልፀዋል።

Share this Post