02
Aug
2021
ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በኢትዮጵያ የአዉስትራሊያ ጊዜያዊ አምባሳደር ከሆኑት ጄኒ ዳን ረን ጋር ውይይት አደረጉ፡፡ በከተማዋ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ በሚያደርጉ ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ ሰፋ ያለ ውይይት አድገናል ያሉት ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በዚህም መግባት ላይ ደርሰናል ብለዋል ። በአዲስ አበባ እና በአዉስተራሊያ ካሉ ከተሞች ጋር የሁለትዮሽ ግንኙነት ፣ በአቅም ግንባታ፣ በንግድና ኢንቨስትመንት ስራዎች ዙሪያ በጋራ ለመስራት መግባባት ላይ መድረሳቸውን ምክትል ከንቲባዋ ገልጸዋል፡፡... ። በተለይም በአውስትራሊያ ባለሀብቶች ድጋፍ ሊገነባ የታሰበውን "የልጆች ተስፋ" የወላጅ አልባና ችግረኛ ህጻናት ማሳደጊያና መንከባከቢያ ማእከልን ግንባታ እውን ለማድረግ እስካሁን ከ200 ሚሊዮን ብር በላይ በመሰብሰቡ ተደስቻለሁ በከተማ አስተዳደሩ ስም አመሰግናለሁ ብለዋል ምክትል ከንቲባዋ ።