በአዲስ አበባ ከተማ ለመከላከያ ሰራዊታችን የሚደረገው ድጋፍ ዛሬም በተለያዩ ክፍለ ከተሞች ተጠናክሮ ቀጥሏል። በቦሌ እና አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የሚገኙ ሴቶች ለጀግናው መከላከያ ሰራዊታ...

በአዲስ አበባ ከተማ ለመከላከያ ሰራዊታችን የሚደረገው ድጋፍ ዛሬም በተለያዩ ክፍለ ከተሞች ተጠናክሮ ቀጥሏል። በቦሌ እና አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የሚገኙ ሴቶች ለጀግናው መከላከያ ሰራዊታችን ደጀንነታቸውን ለማሳየት ስንቅ ዝግጅት አከናውነዋል ። ኢትዮጵያውያን ለጠላት የማይበገሩ ፤በሀገራዊ አንድነታቸው የማይደራደሩ ናቸው ያሉት በስንቅ ዝግጅት የተሳተፉ ነዋሪዎች መከላከያ ሰራዊቱ ከህዝብ ተፈጥሮ ለህዝብ የቆመ የምንግዜም ኩራታችን ነው ብለዋል። በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የወረዳ 03 አስተዳደርም ከስንቅ ዝግጅቱ በተጨማሪ ለሠራዊቱ አራት ድልብ በሬዎችን በስጦታ አበርክተዋል ።

Share this Post