የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ህብረተሰቡን በማስተባበር በያሰባሰበውን ከ1.1 ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመት የገንዘብ እና የአይነት ድጋፍ ለሀገር መከላከያ ሰራዊት አስረከበ፡፡ ምክትል ከንቲባ...

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ህብረተሰቡን በማስተባበር በያሰባሰበውን ከ1.1 ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመት የገንዘብ እና የአይነት ድጋፍ ለሀገር መከላከያ ሰራዊት አስረከበ፡፡ ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ "ኢትዮጵያን ለማዳን እዘምታለሁ" በሚል መርህ በመስቀል አደባባይ በተደረገው መርሐግብር ለኢፌዴሪ ሀገር መከላከያ ሚነስትሩ ዶ/ር ቀነዓ ያደታ እና የሰራዊቱ ከፍተኛ መኮንኖች በተገኙበት አስረክበዋል፡፡ የከተማችን ነዋሪዎች የአሸባሪውን ህወሓት ሴራ ለማክሸፍ እና ለሰራዊቱ ደጀንነቱን ለማሳየት በአጭር ጊዜ በተደረገ እንቅስቃሴ ከ1.1 ቢሊዮን ብር በላይ የገንዘብ ፣የሰንጋ በሬ ፣በግናፍየል እንዲሁም ልዩ ልዩ ቁሳቁሶች ድጋፍ መሰብሰቡን የገለጹት ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ ድጋፉን ላደረጉ የከተማዋ ባለሃብቶች እና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎ...ች ምስጋና አቅርበዋል፡፡ የመከላከያ ሚኒስትር ዶ/ር ቀነአ ያደታ በበኩላቸው የከተማዋ ነዋሪዎች ላደረጉት ድጋፍ ለሰራዊቱ ከሞራልም በላይ ነው፤ለተደረገው ድጋፍም በሰራዊቱ አባላት እና በሚኒስቴሩ ስም ምስጋና አቅርበዋል፡፡

Share this Post