የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግና ተጠሪ ተቋማት በቂርቆስ ወረዳ 09 የ15 አቅመ ደካሞችን ቤት የማደስ ስራ ጀመሩ። የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዎስን ጨምሮ የተጠሪ ተቋማት አ...

የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግና ተጠሪ ተቋማት በቂርቆስ ወረዳ 09 የ15 አቅመ ደካሞችን ቤት የማደስ ስራ ጀመሩ። የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዎስን ጨምሮ የተጠሪ ተቋማት አመራሮች ፣ሰራተኞች እና የቂርቆስ ክፍለ ከተማ አመራሮች የቤት እድሳት ስራውን በይፋ አስጀምረዋል ። የአቅመ ደካሞችን ቤት ማደስ ለነዋሪዎቹ ያለው ትርጉምና ደስታ ወደር የለሽ መሆኑን የገለፁት የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ በዚህ የክረምት በጎ ፍቃድ አገልግሎት የተጠሪ ተቋማት ስራተኞችንም በማስተባበር ከ23 በላይ ቤቶችን አድሰን ለባለቤቶቹ እናስረክባለን ብለዋል። ዛሬ የተጀመረው የቤት እድሳት ስራ የዚህ አካል መሆኑን ጠቅላይ አቃቢ ህጉ ተናግረዋል። በቂርቆስ ክፍለ ከተማ በዘንድሮው የክረምት ወራት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ባለሀብቶችን እና የተለያዩ የፌዴራል ተቋማትን በማስተባበር ከ200 በላይ የአቅመ ደካማ ቤቶችን በማደስ ለነዋሪው ለማስረከብ እየተሰራ ይገኛል ተብሏል ።

Share this Post