"ህይወታችንን ገብረን ኢትዮጵያን እናቆያታለን!" - ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ

 

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አዘጋጅነት መከላከያን ለመደገፍ እና አሸባሪው ቡድን በከፈተው ጦርነት የተፈናቀሉ ዜጎችን ለማቋቋም በተካሄደው ገቢ ማሰባሰባ መርሐግብር ላይ በመገኘት መልዕክት አስተላልፈዋል ።

የዛሬ መቶ አመት አካባቢ ኢትዮጵያዊያን ወራሪ ሲመጣባቸው እንዴትሆነው ነጻ እንዳወጡ ሳስብ ይገርመኛል ፤ከቅርብና ከሩቅ ሲያጠቋም አንገዛም ብለው ኢትዮጵያንዉያን በህብረት ቆመዋል ብለዋል።ኢትዮጵያን ትላንትም ነጻ ነበርን፣ ዛሬም ነጻ ነን፣ ነገም ነጻ እንሆናለን ያሉት ጠቅላይ ሚንስትሩ ኢትዮጵያ የተፈተነችው በአቅሟ ልክ ነው ፤ሌላው ቢሆን በዚህ ልክ አይፈተንም ብለዋል።

የኢትዮጵያ ጠላቶች በተባበረ ክንድ ይሸነፋሉ ፤ለምልሟ ባንድራዋም ከፍ ብሎ የምናይበት ጊዜ ይመጣል ህይወታችንን ገብረን ኢትዮጵያን ለቀጣዩ ትውልድ እናቆያታለን ብለዋል ጠቅላይ ሚንስትሩ።እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊም ሀገሩን የሚወድ ገንዘብ ያለው በገንዘቡ፤እውቀት ያለው በእውቀቱ ፤ጉልበት ያለው በጉልበቱ በተባበረ ክንድ በጋራ እንድንቆም ጠያቂ ብቻ ሳይሆን መላሽም እንድትሆኑ አደራ እላለሁ ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል ።ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወዴት አለ ብለው ለሚጠይቁ ሁሉ ጀልባዋ ላይ ነው ያለው በሏቸው ፤ህዝቡን ወታደሩን አስተባብሮ ነጻ የተረከባትን ሀገር ነጻ ያስረክባል ሲሉ ተናግረዋል ።ኢትዮጵያ አትፈርስም አትበተንም ጠላቶቿን አሸንፋ የአፍሪካ ፈርጥና ምሳሌ ትሆናለች ብለዋል ።

Share this Post