03
Sep
2021
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አብዲ ጸጋዬ በ5ቱ የጳጉሜ ቀናት በከተማዋ ከማዕከል እስከ ወረዳ ድረስ ሀገራዊ እና ከተማ አቀፋዊ ፋይዳ ባላቸው መርሐግብሮች እንደሚከበር አስታውቀዋል፡፡
በአምስቱ የጳጉሜ ቀናትም ኢትዮጵያዊነትን በማጉላት ፣ የተቸገሩ ወገኖችን በመርዳት፤አብሮነትን እና አንድነትን በማጠናከር ፣የሀገር እና የከተማችንን ከገጽታ ከመገንባት እና ከማስተዋወቅ አንጻር ትልቅ አስተዋጽኦ የሚያበረክቱ ሁነቶች መሰናዳታቸውን ሃላፊው ጠቁመዋል፡፡
በዚሁ መሰረት ጳጉሜ 1 የኢትዮጵያዊነት ቀን ፣ጳጉሜን 2 የአገልጋይነት ቀን፣ጳጉሜን 3 የመልካምነት ቀን ፣ጳጉሜን 4 የጀግንነት ቀን እና ጳጉሜን 5 የድል ቃል-ኪዳን ብስራት ቀን ተብለው መሰየማቸውን አቶ አብዲ አመልክተዋል፡፡