መጪውን የመስቀል በዓል በድምቀት ለማክበር ዝግጅት መጠናቀቁን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክስቲያን ጠቅላይ ቤተ ክህነት አስታወቀ::

 

የቤተክህነቱ ምክትል ስራ አስኪያጅ ሊቀ አዕላፍ ቀሲስ በላይ መኮንን በበዓሉ አከባበር ቅድመ ዝግጅት ዙሪያ መግለጫ ስጥተዋል::

ባለፈው ዓመት በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ሳቢያ በጥቂት ሰዎች በዓሉ መከበሩን ያወሱት ምክትል ስራ አስኪያጁ ዘንድሮ ተገቢውን የጥንቃቄ ተግባራት በመከወን በድምቀት ለማክበር ታስቧል ብለዋል::

በታሰበለት ጊዜና ድንቅ የግንባታ ስራ በተጠናቀቀው መስቀል አደባባይ ላይ የሚከበረው በዓሉ ያለምንም ፀጥታ ችግር እንዲጠናቀቅ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ ይገኛል ብለዋል::

የመስቀል በዓሉ በድምቀት እንዲከበር በርካታ የቤተክርስቲያኗ ኮሚቴዎች እየተንቀሳቀሱ ነው ያሉት ምክትል ስራ አስኪያጁ የበዓሉ ስነ ስርዓቶች እስከ ቀኑ 12 ሰዓት ድረስ ብቻ ይከወናሉ ብለዋል::

Share this Post