በከተማዋ ከ30 ሺህ በላይ የአሜሪካ ዶላር ይዞ በሕገ-ወጥ መንገድ ሲያዘዋውር የነበረ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ:: ከ30 ሺህ በላይ የአሜሪካ ዶላር ይዞ በሕገ-ወጥ መንገድ ሲያዘዋውር የነበ...

በከተማዋ ከ30 ሺህ በላይ የአሜሪካ ዶላር ይዞ በሕገ-ወጥ መንገድ ሲያዘዋውር የነበረ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ:: ከ30 ሺህ በላይ የአሜሪካ ዶላር ይዞ በሕገ-ወጥ መንገድ ሲያዘዋውር የነበረ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተጣራበት መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ። ተጠርጣሪው የተያዘው በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ልዩ ቦታው 22 አንድ ተብሎ በሚጠራው ባቡር ጣቢያ ላይ ነው። ግለሰቡ በወቅቱ 30 ሺህ 204 የአሜሪካ ዶላር ይዞ ባቡር ሊሳፈር ሲል በባቡር ጣቢያው ላይ ተመድበው ሲሠሩ የነበሩ የፖሊስ አባላት ባደረጉት ፍተሻ ከነዶላሩ በቁጥጥር አውለውታል። ሕገ-ወጥ የገንዘብ ዝውውር እና የውጪ ሀገራት ገንዘቦችን በሕገ-ወጥ መንገድ የመመንዘር ወንጀል የኑሮ ውድነት እንዲያሻቅብ ከማድረግ ባሻገር በሀገር ኢኮኖሚ ላይ የሚያሳድረው አሉታዊ ጫና ከፍተኛ በመሆኑ ኅብረተሰቡ ይህንን ሕገ-ወጥ ድርጊት ባለመፈፀም እና የሚፈፅሙ አካላትንም ለሕግ አሳልፎ በመስጠት የሚጠበቅበትን ኃላፊነት እንዲወጣ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አሳስቧል።

Share this Post