የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት አስተዋፅኦ ላበረከቱ የጤና ባለሙያዎች እና ክብካቤ ሰራተኞች የምስጋና ዕውቅና ተሰጠ። በዕውቅና መርሐግብር ላይ የተገኙት በምክ...

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ወቅት አስተዋፅኦ ላበረከቱ የጤና ባለሙያዎች እና ክብካቤ ሰራተኞች የምስጋና ዕውቅና ተሰጠ። በዕውቅና መርሐግብር ላይ የተገኙት በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የመንግሥት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ አቶ ጃንጥራር አባይ እንዳስታወቁት በወረርሽኙ ወቅት ግንባር ቀደም በመሆን ወጎኖቻችሁን በመታደግ ላበረከታችሁት አስተዋጽኦ የከተማ አስተዳደሩ ምስጋናና ዕውቅና ይሰጣል ብለዋል ። በቀጣይም የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ከመከላከልና ከመቆጣጠር ባለፈ በወረርሽኙ ምክንያት የሚያጋጥሙ ዘርፈ ብዙ ችግሮችን ለመፍታት የከተማ አስተዳደሩ በትኩረት እንደሚሰራ አቶ ጃንጥራር ጠቁመዋል ። የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዮሃንስ ጫላ በበኩላቸው የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በሀገር አቀፍ ደረጃ ከተመዘገበው ቁጥር በአዲስ አበባ ከተማ ደረጃ ከፍተኛ ቢሆንም ነዋሪዎች በወረርሽኙ ሳቢያ ለከፋ ጉዳት እንዳይጋለጡ የጤና ባለሙያዎች እና የክብካቤ ሰራተኞች የበኩላቸውን በማድረግ እስከ ህይወት መስዋዕትነት በመክፈል የበኩላቸውን አስተዋፅኦ ማበርከታቸው ተናግረዋል ። በከተማ አስተዳደሩ በተዘጋጀው የኮቪድ-19 ምላሽ ለሰጡ እና በመከላከል ተግባር የላቀ አስተዋጽኦ ላበረከቱ የሕክምና ባለሙያዎች ፣ የመንግሥት እና የግል ጤና ተቋማት፣የኮቪድ -19 ማገገሚ ማዕከላት ውስጥ የሚያገለግሉ የክብካቤ ሰራተኞች የዕውቅና ሽልማት ተበርክተዋል ። በተጨማሪም በኮቪድ-19 ተይዘው ያገገሙ የጤና ባለሙያዎች የነበረውን የህክምና ሂደት እና ሰለወረርሽኙ አስከፊነት ምስክርነታቸውን የሰጡ ሲሆን በጤና ባለሙያዎች ለተደረገላቸው የህክምና እርዳታም ምስጋና አቅርበዋል።

Share this Post