የድጋፍ ሰጪ አውቶቡሶች ውል ለተጨማሪ ሶስት ወራት ተራዘመ፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ የድጋፍ ሰጪ አውቶቡሶችን ከመስከረም 4/2014 . ጀምሮ ለሶስት ወራት እስከ ታህሳስ 3/2014 . አራዝሟል፡፡በመዲናዋ ድጋፍ ሰጪ አውቶቡሶች ወደስራ ከገቡ በኋላ በአማካይ 3 መቶ 92 አውቶቡሶች በየቀኑ አገልግሎት እንዲሰጡ በመደረጉ የትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጡ እንዲሻሻል አስተዋጽኦ አበርክተዋል፡፡

በሁሉም አውቶቡሶች ላይ GPS በመግጠም የክትትልና ቁጥጥር የሚደረግ ሲሆን ይህም በቀን በአማካኝ 182 ሺህ ተጠቃሚዎች አገልግሎት በመስጠት የተሳፋሪ የጊዜ ቆይታን በአማካይ 60 ደቂቃ ወደ 12 ደቂቃ ዝቅ በማድረግ አገልግሎት አሰጣጡም እየተሻሻለ መጥቷል፡፡

ማህበራትም በውሉ መሰረት የተቀመጡ የአሰራር ስርዓቶችን ስራ ላይ በማዋል ከዚህ የተሻለ አገልግሎት እንዲኖር ትኩረት ሰጥተው ሊሰሩ እንደሚገባ የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ቢሮ አሳስቧል፡፡የከተማ አስተዳደሩ ከጥቅምት 9/2013 . ጀምሮ ሀገር አቋራጭ አውቶቡሶች በኪራይ የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲሰጡ መደረጉ ይታወሳል

 

Share this Post