በአቶ ደመቀ መኮንን የተመራ ልዑክ በአርባምንጭ ከተማ የልማት ሥራዎችን ጎበኘ

በኢፌዲሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የተመራ ልዑክ በአርባምንጭ ከተማ የተከናወኑ የልማት ሥራዎችን ጎበኘ፡፡

ልዑኩ የሙዝ ማሳ የጋሞ ባይራ ሞዴል 2 ደረጃ ትምህርት ቤት፣ የጋሞ ልማት ማኅበር በመስኖ ያለማውን የበቆሎ ማሳ እና የአርባምንጭ አረንጓዴ ልማት መዝናኛ ፓርክን መጎብኘቱን የጋሞ ዞን ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

በጉብኝቱ የአማራ፣ የኦሮሚያ፣ የሶማሌ፣ የአፋር፣ የደቡብ፣የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ፣ የጋምቤላ፣ የቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ የሲዳማ ክልሎች ርዕሰ መስተዳድሮች እና የአዲስ አበባ እንዲሁም የድሬዳዋ ከተማ ከንቲባዎች ተገኝተዋል፡፡

በጋሞ ባይራ 2 ደረጃ ትምህርት ቤት ግቢ የችግኝ ተከላ መርሐ ግብርም ተካሂዷል፡፡

Share this Post