ለመዲናዋ ሰላምና ጸጥታ መረጋገጥ የሰላም ሰራዊት አባላት ሚና የጎላ መሆኑ ተገለጸ።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ በአዲስ በተቋቋመው የህዝብ ዘርፍ የሰላም ሰራዊት አደረጃጀት ዙሪያ ላይ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አካሂዷል።

የከተማችንን ሰላምና ጸጥታ ለማስፈን የሰላም ሰራዊት በደንብ እና በአዋጅ ማቋቋም አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ከአስፈጻሚ አካላት ጋር የጋራ አድርጎ በቅንጅት መስራት እንደሚገባ በውይይቱ ላይ ተገልጿል።

በውይይት መድረኩ ላይ የአዲስ አበባ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ የሃይማኖትና የሰላም እሴት ዳይሬክተር አቶ ተመስገን እጅጉ እንደገለጹት፡- ህብረተሰቡ በሰላምና ጸጥታ ስራዎች ላይ ሁሉን አቀፍ ተሳትፎ በማድረግ ለከተማዋ ሰላምና ጸጥታ መረጋገጥ የሰላሙ ባለቤት መሆን እንዳለባቸው ተናግረዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኃላፊ ሊዲያ ግርማ የተደራጀው የሰላም ሰራዊት ከጸጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት በከተማችን ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን እያደረገ ያለውን አስተዋጽኦ ቀጣይነት እንዲኖረው ሁሉም ባለድርሻ አካላት በመናበብና በመቀናጀት መስራት ይጠበቃል ብለዋል።

የመድረኩ ተሳታፊዎች በበኩላቸው የአደረጃጀቱ ደንብ በመናበብና በቅንጅት እንዲሁም ሁሉንም ባለድርሻ አካል ባለቤት ማድረግ፣ በመመሪያ በመደገፍ ተፈጻሚ እንዲሆን መደረጉ ይበልጥ ውጤታማ ያደርገዋል ብለዋል።

 

Share this Post