"ሀገሬን እጠብቃለሁ መስዋዕትነት እከፍላለሁ "በሚል ከአዲስ አበባ ከተማ የተውጣጡ በርካታ ወጣቶች የሀገር መከላከያ ሰራዊቱን ለመቀላቀል እና ድጋፍ የመስጠት መርሐግብር እየተካሄደ ነው።

 

በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በመካሄድ ላይ በሚገኘው የወጣቶች የድጋፍ መርሐግብር የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣በአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ መለሰ አለሙ ፣ከፍተኛ አመራሮች እና በሺዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች ተገኝተዋል

የህውሃት ቡድን ኢትዮጵያን ለማፍረስ እያደረገ ያለውን ሴራ ለማክሸፍ ከአዲስ አበባ ከተማ ከሁሉም ከፍለከተሞች የተውጣጡ ሀገር ወዳድ ወጣቶች አሸባሪው ለመፋለም በቆራጥነት ተነስተዋል ።

በዛሬው ዕለትም ህዝባዊ ዘመቻውን ለመምራት ከተለያዩ ክፍለ ከተሞች የተውጣጡ ከ363 አመራሮች እና የሀገር መከላከያ ሰራዊቱን የሚቀላቀሉ በርካታ ወጣቶች ሽኝት የሚደረግላቸው ይሆናል።

አካባቢዎን ይጠብቁ!

ወደ ግንባር ይዝመቱ!

መከላከያን ይደግፉ!

Share this Post