"ለኢትዮጽያ እና ለነፃነታችን ሁላችንም ዘማቾች ነን!"ከንቲባ አዳነች አቤቤ

"ሀገሬን እጠብቃለሁ መስዋዕትነት እከፍላለሁ "በሚል ከአዲስ አበባ ከተማ የተውጣጡ እና ህዝባዊ ዘመቻውን ለመምራት 363 አመራሮች ወደ ግንባር ሽኝት ተደርጎላቸዋል ።በሽኝት መርሐግብሩ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ እኛ እያለን አሸባሪው የህውሃት ጁንታ ቡድን እና ተላላኪዎቹ መቼም ቢሆን ኢትዮጵያን አያፈርሷትም ብለዋል ።ለኢትዮጵያ ሉአላዊነት እና ለህዝቦቿ አንድነት ሁላችንም እንታገላለን ፤ሞትም ከሆነ ለኢትዮጵያ የክብርም ክብር በመሆኑን ከንቲባዋ ገልጸዋል ።

ለኢትዮጽያ እና ለነፃነታችን እኛ ሁላችንም ዘማቾች ነን ያሉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ያለ መስዋእትነት ድል የለም ፤በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ መሸነፍ የለም አሁንም አንሸነፍም ብለዋል።ጁንታው አይደለም ደሴ ፤የትም ቢመጣ መጨረሻቸው መቃብር ነው ያሉት ከንቲባዋ በገቡበት ሁሉ እቀብራቸዋለን፤ ከገቡበት መሬት አይወጡም እዛው ባሉበት ይቀበራሉ ብለዋል።በዛሬው ዕለትም በመጀመሪያ ዙር 363 አመራሮች ሽኝት የተደረገላቸው ሲሆን በቀጣይ ዙሮችም በርካታ አመራሮች ምዝገባ እያካሄዱ ይገኛሉ።

Share this Post