"መልካም ዕድል ለኢትዮጵያ ልጆች!!"ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ዛሬ ከሰዓት በጃፓን ቶኪዮ ኦሎምፒክ ውድድር የኢትዮጵያን ሰንደቅዓላማ በዓለም አደባባይ ከፍ ለማድረግ ለሚፋለሙት አት...

"መልካም ዕድል ለኢትዮጵያ ልጆች!!"ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ዛሬ ከሰዓት በጃፓን ቶኪዮ ኦሎምፒክ ውድድር የኢትዮጵያን ሰንደቅዓላማ በዓለም አደባባይ ከፍ ለማድረግ ለሚፋለሙት አትሌቶቻችን መልካም ዕድል እመኛለሁ ብለዋል ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ። ክብር ኢትዮጵያን በተሰማሩበት መስክ ከፍ ከፍ ለማድረግ ለሚታትሩ ሁሉ ሲሉ መልዕከታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ በቶኪዮ ኦሎምፒክ ዛሬ ከሰዓት ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ውድድራቸውን የሚያካሂዱ ሲሆን ከቀኑ 9:15 ሰዓት ላይ 3000 ሜትር መሰናክል ወንዶች ለሜቻ ግርማ እና ጌትነት ዋለ ይሮጣሉ፡፡ በተመሳሳይ 9፡40 ሰዓት በሴቶች 5000 ሜትር ጉዳፍ ፀጋዬ፣ ሰንበሬ ተፈሪ እና እጅጋየሁ ታዬ ለኢትዮጵያ ወርቅ ለማምጣት ብርቱ ፉክክር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

Share this Post