"አዲስ አበባ፡የኢትዮጵያ የድል ነጸብራቅ" በሚል የ2014 ዓ.ም አዲስ ዓመት መቀበያ በተለያዩ መርሐግብሮች ለማክበር ዝግጅት መደረጉ ተገለጸ፡፡

 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን /ቤት ኃላፊ አቶ አብዲ ጸጋዬ 5 የጳጉሜ ቀናት በከተማዋ ከማዕከል እስከ ወረዳ ድረስ ሀገራዊ እና ከተማ አቀፋዊ ፋይዳ ባላቸው መርሐግብሮች እንደሚከበር አስታውቀዋል፡፡

በአምስቱ የጳጉሜ ቀናትም ኢትዮጵያዊነትን በማጉላት የተቸገሩ ወገኖችን በመርዳት፤አብሮነትን እና አንድነትን በማጠናከር ፣የሀገር እና የከተማችንን ከገጽታ ከመገንባት እና ከማስተዋወቅ አንጻር ትልቅ አስተዋጽኦ የሚያበረክቱ ሁነቶች መሰናዳታቸውን ሃላፊው ጠቁመዋል፡፡

በዚሁ መሰረት ጳጉሜ 1 የኢትዮጵያዊነት ቀን ፣ጳጉሜን 2 የአገልጋይነት ቀን፣ጳጉሜን 3 የመልካምነት ቀን ፣ጳጉሜን 4 የጀግንነት ቀን እና ጳጉሜን 5 የድል ቃል-ኪዳን ብስራት ቀን ተብለው መሰየማቸውን አቶ አብዲ አመልክተዋል፡፡

 

Share this Post