06
Dec
2021
በሩቅና በቅርብ ሀይሎች የተጋረጠብንን የህልውና አደጋ በአንድነት በመመከትና በማሸነፍ፤ በድል አድራጊነት ፤ በኢትዮጵያ አደባባይ እንደምንቆም በማመን ከያላችሁበት ድምፃችሁን ከፍ አድርጋችሁ የኢትዮጵያን እዉነት በመላው አለም እያሰማችሁ ያላችሁ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ደራሽ ልጆች፤ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን ዶክተር አብይ አህመድ መጪዉ የገና በአልን በአገራችሁ ኢትዮጵያ ከያላችሁበት ተሰባስባችሁ በአንድነት እንድታከብሩ ባቀረቡት ጥሪ መሰረት የእናንተ የሁላችሁም ዞሮ መግቢያ ከተማችሁ "አዲስ አበባ " እንደ ስሟ አበባ መስላ ፤ የሰላም አየር እየተነፈሰች ፤ በደስታና በናፍቆት ልጆቼ እንኳን ደህና መጣችሁ ብላ ልትቀበላችሁ ቅድመ ዝግጅቶቿን አጠናቃ ትጠብቃችኋለች!!
#ኢትዮጵያ በሀቀኛ ልጆቿ ያላሰለሰ ጥረትና መስዋዕትነት ለዘላለም ተከብራ ትኖራለች ፤
ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን አብዝቶ ይባርክ!!
የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ