17
Aug
2021
"ኪነ ጥበብ ምንጊዜም ከኢትዮጵያ ጀግንነት ጋር ናት"፦ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ኪነ ጥበብ ምንጊዜም ከኢትዮጵያ ጀግንነት ጋር ናት ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በወታደራዊ ማሰልጠኛዎች ዝግጅቶችን ላቀረቡ የኪነጥበብ ባለሙያዎች ምስጋና አቅርበዋል ። "ኢትዮጵያን ለማዳን እዘምታለሁ መቼም፣ የትም፣ በምንም" በሚል መሪ ቃል የአዲስ አበባ ከተማ አራቱ ቴአትር ቤቶች፣ የብሔራዊ ቴአትር፣ የኦሮሞ የባህል ማዕከል የኪነ ጥበብ ባለሞያዎች በወታደራዊ ማሠልጠኛዎች ተገኝተው ዝግጅቶችን አቅርበዋል። ኪነ ጥበብ ምንጊዜም ከኢትዮጵያ ጀግንነት ጋር ናት በማለትም ጠቅላይ ሚኒስትሩ መልእክታቸውን አስፍረዋል፡፡ በዚህም ዝግጅቶቹን ላቀረቡ የኪነ ጥበብ ባለሞያዎች ምስጋናቸውን ያቀረቡት ዶ/ር አብይ አህመድ ሌሎችም ከያንያን አርአያነታችሁን እንደሚከተሉ ተስፋ አደርጋለሁ ብለዋል።