"የነጩ ፓስታ ጎርፍ ወደ ነጩ ቤተመንግሥት" ሀገር አቀፍ ደብዳቤ የመጻፍ እና የፊርማ ማሰባሰብ ንቅናቄ መርሐግብር በቅርቡ በይፋ መጀመሩ የሚታወስ ነው።

የውጪ ሀገራት በተለይ የአሜሪካ መንግስት በኢትዮጵያ የውስጥ ጉዳይ የሚያደርገውን ጣልቃ ገብነት እና የኢትዮጵያን እውነት ለዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ ለማስረዳት ያለመ ሀገር አቀፍ ደብዳቤ የመጻፍ እና የፊርማ ማሰባሰብ ንቅናቄ መርሐግብር በቅርቡ በይፋ መጀመሩ የሚታወስ ነው።በዛሬው ዕለትም ምክትል ከንቲባ / አዳነች አቤቤ እና የካቢኔ አባላት "የነጩ ፓስታ ጎርፍ ወደ ነጩ ቤተመንግሥት" በሚል ደብዳቤ የመጻፍ እና ፊርማ የማሳረፍ መርሐግብር አካሂደዋል፡፡

ምክትል ከንቲቤ / አዳነች አቤቤ በመርሐ-ግብሩ ላይ እንደተናገሩት የኢትዮጵያ ወጣቶች የሀገሪቱን እውነት ዓለም እንዲረዳው ለማድረግ የጀመሩት "የነጩ ፖስታ ጎርፍ ወደ ነጩ ቤተመንግሥት" የተሰኘው ሀገር ዓቀፍ ንቅናቄ ከምንም በላይ ኢትዮጵያ የወጣቶቿን ሁለንተናዊ ድጋፍ በሁሉም መስክ በምትሻበት ጊዜ በመሆኑ ሊበረታታ እና ሊመሰገን የሚገባው ተግባር ነው ብለዋል፡፡ የሕውኃት አሸባሪ ቡድን በኢትዮጵያ ሕዝብና ወጣቶች ላይ እጅግ አሰቃቂ የሰብአዊ መብት ጥሰት አድርሷል ፤የኢትዮጵያ ሀብት ዘርፏል ፤ይህ ሁሉ አልበቃ ብሎት ጥቅምት 24 በሰሜን እዝ ላይ ጥቃት ፈጽሟ ፣በመላ ሀገሪቱም የሽብር ወንጀሎችን እየፈጸመ ይገኛል ብለዋል ምክትል ከንቲባዋ

ቡድኑ በአሁኑ ወቅትም በአፋር እና አማራ ክልሎች ላይ ወረራ በመፈጸም ሰብዓዊ ቀውስ እያደረሰ ይገኛል ያሉት ምክትል ከንቲባዋ ይሕን የቡድኑን እኩይ የአሸባሪነት ተግባር ለዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ ልናሳውቅ ይገባል ብለዋል

 

Share this Post