"የከተማችን ህዝባዊ ሰራዊት የከበረ ምስጋናዬ በያላችሁበት ይድረሳችሁ " ከንቲባ አዳነች አቤቤ.

 

የአዲስአበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ

ማምሻዉን በተለያዩ የአዲስአበባ አካባቢዎች በመንቀሳቀስ የተለያዩ ወጣቶች የአካባቢያቸውን ሰላምና ፀጥታ በማስጠበቅ ረገድ እያደረጉት ያለውን እንቅስቃሴ ተመልክተዋል ።ይህንን አስመልክቶ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸዉ ላይ ባሰፈሩት አስተያየት በተለያዩ የመዲናችን አካባቢዎች ተንቀሳቅሼ ህዝባዊ ሰራዊት የአካባቢያቸውን ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ ያለአንዳች መዘናጋት በተጠንቀቅ የአካቢያቸዉን ሰላም እያስጠበቁ ፤ አካባቢያቸውን እየቃኙ እያደረጉት ያለውን የተናበበ ፤ የተቀናጀ እንቅስቃሴ ተመልክቻለዉ " ብለዋል።

አያይዘውም ይህ የወጣቶች ስራ ከተጀመረ ወዲህ የየአካባቢያውን ሰላምና ደህንነት ከማስጠበቅ በተጨማሪ በተለያዩ አካባቢዎች ይሰሩ የነበሩ የንጥቂያና መሰል ወንጀሎች መቀነስ ስራቸው ምን ያህል ፍሬያማ እንደሆነ ማሳያ ነዉ በማለት የወጣቶቹን ተግባር አበረታተዋል ።

በተጨማሪም የየአካባቢው ማህበረሰብም ለወጣቶቹ ምግብና አስፈላጊ ቁሳቁሶችን በማቅረብ ከጎናቸው በመቆም በአቅማችሁ እናበርታችሁ ማለታችሁ የሚያስመሰግን አጋርነት ነዉ ያሉ ሲሆን ወጣቶች እንዲሁም ወጣቶቹን በተለያየ መንገድ እየደገፋችሁ ያላችሁ የየአካባቢው ነዋሪዎች እያበረከታችሁት ላለው ታላቅ ተግባር ሁላችሁንም በራሴና በከተማው አስተዳደር እንዲሁም በመላው ሰላም ወዳዱ የከተማችን ነዋሪዎች ስም ሳላመሰግን አላልፍም ፤

ወጣቶቻችን እያደረጋችሁት ባለዉ ተግባር ኮርተንባቹሀል ፤ በማለት ለወጣቶቹ ያላቸውን አክብሮት ገልፀዋል ።

Share this Post