30
Jul
2021
"የከተማ አስተዳደሩ በባለፈው በጀት ዓመት ለትምህርት ምገባ ከ1.2 ቢሊዮን ብር በላይ በመመደብ ከ600 ሺህ በላይ ተማሪዎችን ተጠቃሚ አድርጓል":- ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በባለፈው በጀት ዓመት ለትምህርት ምገባ ከ1.2 ቢሊዮን ብር በላይ በመመደብ በከተማዋ እና በዙሪያዋ የሚገኙ ከ600 ሺህ በላይ ተማሪዎችን የምገባ ፕሮግራም ተጠቃሚ በማድረግ ቀደም ሲል ከነበረው በጀት ዓመት ተጠቃሚዎቹን በእጥፍ በማሳደግ ለክልሎች ተሞክሮ መሆን መቻሉን ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገልጸዋል። በተጨማሪም የከተማ አስተዳደሩ የዜጎችን ፍትሃዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በተለያዩ 5 ክፍለ ከተሞች በቀን አንድ ጊዜ መመገብ የማይችሉ ዜጎችን በመለየት የምግብ አገልግሎት እንዲያገኙ በአንድ ጊዜ 1000 ዜጎችን ማስተናገድ የሚችሉ የመ...መገቢያ ማዕከላትን በማቋቋም በሺዎች የሚቆጠሩ የጎዳና ተዳዳሪዎች እና በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ያሉ ዜጎችን ተጠቃሚ ማድረግ ችሏል ተብሏል። የተማሪዎች ምገባ መርሐግብርን ጨምሮ የከተማ አስተዳደሩ በምገባ ዘርፍ የጀመራቸው ስራዎች ለሌሎች ሀገራት ምርጥ ተሞክሮ እንደሚሆኑ በማመን ትላንት በጣሊያን ሮም ከተማ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት አዘጋጅነት በተካሄደው የዓለም ስነ ምግብ ኮንፈረንስ ላይ በተሞክሮነት ቀርቧል። ይህ ስራ ተማሪዎች የተመጣጠነ ምግብ እንዲያገኙ ከማድረጉ እና የተማሪዎችን ወጤት በማሳደግ የመድገምና የማቋረጥ ምጣኔን በከፍተኛ ደረጃ መቀነስ ከመቻሉ ባለፈ፣ በምገባ ፕሮግራሙ ምግብ በማብሰል ስራ ከ10 ሺህ በላይ ለሚሆኑ እናቶች የስራ ዕድል በመፍጠር ቋሚ ገቢ እንዲያገኙ ማድረጉን ምክትል ከንቲባዋ አስታውቀዋል ።