ሀሰተኛ መረጃዎችን በመመከትና ለነዋሪዎች ወቅታዊ እና ትክክለኛ መረጃ እንዲደርስ የኮሙኒኬሽን እና ህዝብ ግንኙነት ባለሙያዎች ሚና ከፍተኛ ነው ተባለ።

 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ቢሮ በወቅታዊ ሀገራዊ እና ከተማ አቀፋዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከሴክተር ፣ የክፍለ ከተማ እና የወረዳ ኮሙኒኬሽን አመራሮች ጋር ውይይት አካሂዷል ።የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ አቶ ዮናስ ዘውዴ በውይይት መድረኩ እንደገለፁት ሀገሪቷ ችግር ውስጥ ባለችበት በዚህ ወቅት ለህብረተሰቡ ወቅታዊ እና ትክክለኛ መረጃ ተደራሽ በማድረግና የጠላትን የተሳሳተ ፕሮፓጋንዳ በመመከት በትክክለኛ መረጃ የዳበረ ማህበረሰብ ለመፍጠር ቢሮው ከኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች ጋር ከመቼውም ጊዜ በላቀ ሁኔታ እንደሚሰራ ገልጸዋል ።ሀሰተኛ መረጃዎችን በመመከትና ለነዋሪው ወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮችን በተለያዩ የኮሙኒኬሽን አግባቦች ተደራሽ በማድረግ የኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች ሚና ከፍተኛ መሆኑን ኃላፊው ተናግረዋል፡፡

በዚህም የተሳሳቱ መረጃዎችን በመለየት ማህበረሰቡ ትክክለኛ መረጃ እንዲደርስው ቢሮው ከሚዲያ አካላት እና ባለሙያዎች ጋር ተቀራርቦ እና ተቀናጅቶ እንደሚሰራም አቶ ዮናስ አመልክተዋል ።በተለይ በማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች የሚሰራጩ የተሳሳቱ መረጃዎችን በተቀናጀና በተደራጀ መንገድ በመመከትና ህብረተሰቡ ትክክለኛ መረጃ እንዲደርሰው የኮሙኒኬሽን እና ህዝብ ግንኙነት ባለሙያዎች በላቀ ሁኔታ ሊሰሩ ይገባል ብለዋል።በመድረኩም በአዲስ አበባ ከተማ ደረጃ የሚከናወኑ የህዝብ ተሳትፎ እና የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ ዙሪያ ከኮሙኒኬሽን አመራሮች ጋር ውይይት ተደርጓል ።

Share this Post