ሀገራችን የገጠማትን ዲፕሎማሲያዊ ጫና በማህበራዊ ሚዲያ በሚተላለፍ መልዕክቶች መመከት እንደሚቻል የአዲስ አበባ ከተማ ኮሙኒኬሽን ቢሮ በም/ ቢ/ኃላፊ ማዕረግ የህዝብ ግኑኝነት ሚዲያና ጥናት ምርምር ዳይሬክተር አቶ ሁሴን ዝናብ አስታወቁ።

 

 

በሀገራዊ ወቅታዊ ጉዳይ፣ በቀውስ ጊዜ ተግባቦት እና ማህበራዊ ሚዲያ በሀገራዊ ሁለተናዊ ለውጥ በሚኖረው ጠቀሜታ ላይ በአዲስ አበባ ለሚገኙ የኮሙኒኬሽን አመራሮች እና የህዝብ ግንኙነት ባለሙያዎች ስልጠና በመሰጠት ላይ ይገኛል።

በአሁኑ ወቅት ሀገራችን የገጠማትን ዲፕሎማሲያዊ ጫና በማህበራዊ ሚዲያ አውድ በመዝመት የዜግነት ግዴታን በመወጣት እውነታውን ደጋግሞ በመግለፅ መመከት እንደሚቻል ነው አቶ ሁሴን ዝናብ የተናገሩት።በዚህም ባለፉት ሶስት ወራት በተሰሩ የኮሙኒኬሽን ስራዎች ከውጭም ከውስጥም የተከፈተብንን የሀሰት ፕሮፖጋንዳ እና ዲፕሎማሲያዊ ጫና መመከት ችለናል ብለዋል።የተከፈተብንን ጦርነት በሰላም ወዳድ ልጆቿ የድል የበላይነትን መውሰድ ችለናል ያሉት ኃላፊው እንደ ሀገር የገጠመንን የሀስት የፕሮፓጋንዳ ዘመቻ በዘላቂነት ለመመከትም የኮሙኒኬሽን ቢሮ የዘርፉን አቅም በስልጠና የማሳደግ ፥ምቹ የስራ ሁኔታን ለመፍጠር ግብአት የማሟላት ሰራ ትኩረት ተሰጥቶት እንደሚሰራም የቢሮው ኃላፊው ገልፀዋል።

Share this Post