ሀገርን ለማፍረስ የተነሱ አሸባሪዎች በመቀልበስ የሀገራችን ክብር እና ነጻነቷ እንዲቀጥል በትብብር መስራት የሁላችንም ሀላፊነት ነው ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለፁ::

 

የአዲስ አበባ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ በወቅታዊ ጉዳይ ላይ በአዲስ አበባ ውይይት አካሂደዋል፡፡በውይይት መድረኩ ላይ ተገኝተው መልእክት ያስተላለፉት የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ሀገራችን አሁን የገጠማት ፈተና በአይነቱ ውስብስብ ቢሆንም ለዘመናት በብዙ ፈተና ውስጥ አልፋ እዚህ የደረሰች ጠንካራ ሀገር እንደመሆንዋ ክብሯን ለማስቀጠል የሁላችንንም ሀላፊነት እንደሚጠይቅ ተናግረዋል፡፡ኢትዮጵያ ታፍራና ተከብራ የጸናችው በልጆችዋ ጠንካራ ትግል ብቻ ሳይሆን የፈጣሪ ኪዳን ያላት ሀገር በመሆንዋ ጭምር መሆኑን ከንቲባዋ ተናግረዋል::

ሀገራችን በውስጥ ባንዳና ታሪካዊ ጠላቶቻችን ትፈተን ይሆን እንጂ አትፈርስም ብለዋል፡፡ከንቲባ አዳነች የሀይማኖት ተቋማት በየቤተ እምነቶቻቸው ስለሀገራችን ሰላም በመስበክ የአብሮነት ስሜት ፥ በስነምግባርና በሰላም እሴት ግንባታ ላይ እያደረጉ ያሉትን አስተዋጽኦ ይበልጥ አጠናክረው በማስቀጠል ሀላፊነታቸውን እንዲወጡም ጥሪ አቅርበዋል ::በውይይቱ ላይ የተሳተፉት የሀይማኖት አባቶችም በሀገራችን ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን፤ የመቻቻልና የመከባበር እሴቶች እንዲጎለብቱ በየቤተ እምነቶቻቸው በማስተማር የጀመሩትን ስራ አጠናክረው በማስቀጠል ሀገራዊ አንድነትን በሚያጠናክሩና ለነገዋ ኢትዮጵያ ራእይ ያለው ትውልድ ለማነጽ በትኩረት እንደሚሰሩም ተናግረዋል፡፡

 

 

Share this Post