"ኢትዮጵያ የኮቪድ -19 ወረርሽኝ ተፅእኖን ልትቋቋም የቻለችው የጤና ባለሙያዎች ከራሳቸው በፊት ለዜጎቻችን ቅደሚያ በመስጠታቸው በመሆኑ የላቀ ምስጋና ይገባቸዋል" ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ
የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በኢትዮጵያ ከተከሰተ ጊዜ ጀምሮ አስተዋፅኦ ላበረከቱ የጤና ባለሙያዎች እና ሰራተኞች ሀገር አቀፍ የምስጋናና የእውቅና መርሐግብር በአዲስ አበባ ከተማ ወዳጅነት አደባባይ ተካሂዷል ።
በሀገር አቀፍ የምስጋናና የእውቅና መርሐግብር ላይ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ፣የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ ፣ሚኒስትሮች ፣የጤና ዘርፍ አመራሮች እና ባለሙያዎች ተገኝተዋል ።
የጤና ባለሙያዎች የኮቪድ -19 ወረርሽኝ ወደ ኢትዮጵያ ከገባበት ጊዜ ጀምሮ ከራሳቸው በፊት ለዜጎቻችን ቅደሚያ በመስጠት ላደረጉት መስዋዕትነት የላቀ በመሆኑ ምስጋና እንደሚገባቸው ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በመርሐግብሩ ላይ ገልጸዋል ።
የጤና ሚኒስትሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ በበኩላቸው የጤና ባለሙያዎች ለሀገርና ለህዝብ እየከፈሉት ላለው መስዋዕትነት መመስገን ይገባቸዋል በቅንጅት በመስራቱም ኮቪድ-19 የሚያደርሰውን ጉዳት ለመቀነስ መቻሉን ገልጸዋል፡፡
ዛሬ የተጀመረው ሀገር አቀፍ የጤና ባለሙያዎችና ሰራተኞች የእውቅናና የምስጋና መረሃ-ግብር እስከ ሐምሌ 17 ቀን 2013 ዓ.ም በተለያዩ ክልሎች የሚቆይ እንደሆነም ተጠቁሟል።