ለመጪው የዘመን መለወጫ በዓል በተመጣጣኝ ዋጋ ለማቅረብ እየተሰራ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ህብረት ስራ ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡

ለመጪው የዘመን መለወጫ በዓል የኢንዱስትሪና የግብርና ምርቶችን በሸማች ህብረት ስራ ማህበራት በኩል በተመጣጣኝ ዋና ለማቅረብ እየተሰራ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ህብረት ስራ ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡2014 ዘመን መለወጫ በዓል የኢንዱስትሪና የግብርና ምርቶችን ለሸማቹ ማህበረሰብ በተመጣጣኝ ዋጋ ለማቅረብ እየተሰራ መሆኑን የአዲስ አበባ ህብረት ስራ ማህበራት ኤጀንሲ ምክትል ዳይሬክተር አቶ ሲሳይ አረጋ አስታውቀዋል፡፡

የኤጀንሲው ምክትል ዳይሬክተር አቶ ሲሳይ አረጋ በሰጡት መግለጫ እንደገለጹት ከተለያዩ ክልሎች የኢንዱስትሪና የግብርና ምርቶችን ከሚያመርቱ ህብረት ስራ ማህበራት እና ዩኒየኖች ጋር የገቢያ ትስስር መፈጠሩን ተናግረዋል፡፡በበዓል ወቅት የህብረተሰቡን ፍላጎት መሠረት በማድረግ እስካሁንም የቁም እንስሳትና የእንስሳት ተዋፆ ውጤቶች ፣ቀይ ሽንኩትር፣ በሬ፣ በግ፤ ፍየል ፣ዶሮ፣ እንቁላል ለሸማቹ በተመጣጣኝ ዋጋ ለመሸጥ በበቂ ሁኔታ ምርት ማቅረባቸውን የኤጀንሲው ምክትል ዳይሬክተር አቶ ሲሳይ አረጋ ተናግረዋል

ሸማቹ ማህበረሰብ በአዲስ አበባ ከተማ በሁሉም አካባቢዎች በሚገኙ 148 ህብረት ስራ ማህበራትና በአስር ዩኒየኖች ምርቶቹን መሸመት እንደሚችሉም ገልፃል።

ለመጪው አዲስ ዓመት የዘመን መለወጫ በዓል በሁሉም ሊኳንዳ ቤቶች 156 የእርድ በሬዎች መቅረባቸውንም አቶ ሲሳይ አረጋ አስታውቀዋል፡፡

Share this Post