ለትራፊክ እንቅስቃሴ አስቸጋሪ በሆኑ መንገዶች አስቸኳይ የጥገና ስራ በማከናወን ላይ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን አስታወቀ ። የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን...

ለትራፊክ እንቅስቃሴ አስቸጋሪ በሆኑ መንገዶች አስቸኳይ የጥገና ስራ በማከናወን ላይ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን አስታወቀ ። የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ከክረምት ወራት ጋር ተያይዞ የተቦረቦሩ እና ለትራፊክ እንቅስቃሴ አመቺ ያልሆኑ ቦታዎችን በመለየት ገረጋንቲ እና ሰብ ቤዝ በመሙላት ጊዜያዊ የመንገድ ጥገና ስራዎችን በማከናወን የተሻለ የትራፊክ እንቅስቃሴ እንዲኖር በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ ጊዜያዊ የጥገና ስራ እየተከናወነባቸው ከሚገኙ አካባቢዎች መካከል ከጀሞ ሚካኤል - ሳሪስ አቦ፣ ላፍቶ 58 አካባቢ፣ ብሔረ ፅጌ አካባቢ፣ ከገርጂ ሮባ ወደ ጃክሮስና ጊዮርጊስ ቤ/ክ መሄጃ፣ ከአደይ አበባ ስታዲየም - ቦሌ መድኃኒዓለም፣ ጃክሮስ ጉና አካባቢ፣ ከስድስት ኪሎ - ፈረንሳይ፣ ከሆላንድ ኤምባሲ - ጦርኃይሎች፣ ዊንጌት አ...ደባባይ፣ ልደታ ፍርድ ቤት ድልድይ ስር፣ ጌቱ ኮሜርሻል ጀርባ አካባቢዎች የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ በቀጣይም የክረምቱ ወቅት ተገባዶ መደበኛው የመንገድ ጥገና ሥራ እስኪጀመር ድረስ ከክረምት ጋር በተያያዘ በመንገዶች ላይ ሊከሰት የሚችል የጐርፍ ስጋትን የመከላከልና በተለያዩ ምክንያቶች በመቦርቦራቸው ለትራፊክ እንቅስቃሴ አመቺ ያልሆኑ አስፋልት መንገዶችን በመለየት ጊዜያዊ የጥገና ስራዎችን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ባለስልጣኑ ገልጿል ፡፡

Share this Post