26
Nov
2021
ወ/ሮ ቦጋለች ከበደ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሀገር ሉአላዊነትን ለማስከበር ወደ ግንባር ዘምተው ዝም ብዬ ማየት የለብኝም በማለት የመኖሪያ ቤታቸዉን በመሸጥ ለሀገር መከላከያ ሠራዊት የ2 ሚሊየን ብር የገንዘብ ድጋፍ አደረጉ።
አገር ከሌለ ሁሉም ነገር የማይቻል በመሆኑ፤ በቤት ለመኖር ቅድሚያ አገርን በክብር ማኖር ይገባል ያሉት ወ/ሮ ቦጋለች÷ ቤታቸውን ሸጠው ለኢትዮጵያ ህልውና እየተፋለመ ለሚገኘው ጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊት ለግሰዋል የዘገበው የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ነዉ።
አካባቢዎን ይጠብቁ!
ወደ ግንባር ይዝመቱ!
መከላከያን ይደግፉ!