በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ሀና የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት የሚማሩ ተማሪዎች በምግብ ተመርዘዋል ተብሎ እየተሰራጨ ያለው መረጃ ሀሰት ነው ።

 

ከተማሪዎቹ መካከል ሁለት ተማሪዎች አጥወለወለን ብለው የወደቁ ሲሆን ሌሎች ተማሪዎች ልጆቹን በማየታቸው የህመም ስሜት ተሰምቷቸዋል።የወደቁትንና ሌሎች ተማሪዎችን ጨምሮ ወደ ህክምና በመውሰድ ምርመራ የተደረገላቸው ሲሆን ተማሪዎቹ የምግብ መመረዝም ሆነ ሌላ ምንም አይነት ህመም ስላልተገኘባቸው ወደ ቤታቸው ተመልሰዋል።ከምግብ መመረዝ ጋር የተያያዘ ምንም አይነት ችግር የሌለ በመሆኑ የተማሪ ወላጆች እንዲረጋጉ እና በሀሰተኛ መረጃዎች እንዳይታለሉ እንገልፃለን ።

Share this Post