* ዳያስፖራው የሀገሩን ክብር ለመጠበቅ በዓለም አደባባይ የተጫወተው የአምባሳደርነት ሚና ከፍተኛ ነው ፤
* ዳያስፖራው ለእናት ሀገሩ ጥሪ የሰጠው ምላሽ አኩሪ መሆኑን እና ያሳየው ፅናትም ማሸነፍን ከነ ሙሉ ክብሩ የሚያጎናፅፍ የአንድነት ካባ ሆኖ የሚታይ ነው ፤
* ኢትዮጵያን ለማፍረስ የተባበሩት የውስጥ እና የውጭ ኃይሎች የተለያዩ ጫና ቢያደርጉም በመላው ዓለም የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ፣ “#NoMore” /በቃ/ ብለው በያሉበት ሀገር ያሰሙት ድምፅ ከኢትዮጵያ አልፎ የመላዉ አፍሪካውያን ንቅናቄ ሆኗል ፤
* ስለ ዳያስፖራ ሲነሳ መሪዎቹን ማሸማቀቅ እና የፖለቲካ ሽኩቻ ማሳያ መሆኑ ዛሬ ላይ ታሪክ ሆኗል ፤
* ባይተዋርነት ነግሶ ኢትዮጵያውያን እዚህ እና እዚያ ሆነን መራራቃችን ቀርቷል ፤ ይህ ደግሞ በታሪካችን አዲስ ምዕራፍ ነው ፤
* ኢትዮጵያ የተሠራችበት ውቅር ከቃል በላይ ነው ፣ ለእርሷ የተሰጠ በልጆቿ ደም ውስጥ ብቻ ያለ ከሌሎች ዓለም ሁሉ የተለየ አንዳች ልዩ ፀጋ አላት ፤
* ኢትዮጵያ ትፈርሳለች የሚለውን ብሂል ልጆቿ አፍርሰውታል ፤ በጀግንነት እየወደቁ ቀና ማለትን አሳይተናል ፤ ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት አሸንፋለች ፤
* አዲስ አበባም እንደተሟረተባት ሳይሆን ሰላም መሆኗን በግልጽ እያሳየች ነዉ ፤
* ዳያስፖራው በሀገሩ በሚያደርገው ቆይታ የሀገሩን ምርት እንዲገዛ እና የበኩሉን ሚና እንዲጫወት አደራ እላለሁ ፤
* ኢትዮጵያ የምትበለጽገው በልጆቿ ጥረት በመሆኑ ሁላችንም በጋራ ልንቆም ይገባል ፤ ብለዋል ።