16
Sep
2021
ቢሮዉ ይፋ ባደረገው መረጃ መሰረት በአዲስ አበባ ባሉ ትምህርት ቤቶች ትምህርት ጥቅምት 1 ቀን 2014 ዓ.ም. የሚጀመር ሲሆን፤ ሐምሌ 15 ደግሞ ትምህርት የሚጠናቀቅበትና ትምህርት ቤቶች ለእረፍት ዝግ የሚሆኑበት እንደሆነ ተገልጿል። በመርሀ ግብሩ መሰረት መምህራን እስከ መስከረም 18 ቀን 2014 ዓ.ም ድረስ ሪፓርት እንደሚያደርጉ ታውቋል።
99 ቀናት ያሉት የመጀመሪያው መንፈቅ ዓመት ትምህርት የማጠቃለያ ፈተናው ከየካቲት 14 እስከ የካቲት 18 ድረስ እንደሚሠጥ ተገልጿል፡፡
የሁለተኛው መንፈቅ ዓመት ትምህርት ከየካቲት 28 እስከ ሀምሌ 15 የሚሰጥ ሲሆን 99 የትምህርት ቀናት እንዳሉት ነው የተገለጸው፡፡
የ8ኛ ክፍል ፈተና ለሶስት ቀናት የሚሰጥ ሲሆን የማስፈተኛ ጣቢያ የሆኑ ትምህርት ቤቶች ብቻ ዝግ ይደረጋሉ ያለው ትምህርት ቢሮው የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና የሚሰጥበት ቀን ተወስኖ ሲሰጥ ለ2013 እና ለ2014 ለእያንዳንዳቸው 4 ቀናት የመፈተኛ ሲሆኑ የማስፈተኛ ጣቢያ የሆኑ ትምህርት ቤቶች ብቻ ዝግ ይደረጋሉ ተብሏል፡፡
የሁለተኛው መንፈቅ ዓመት ትምህርት የማጠቃለያ ፈተና ከሰኔ 30 እስከ ሃምሌ 5 ድረስ የሚሰጥ ሲሆን የ2014 ትምህርት ዘመን ሃምሌ 15 ቀን 2014 ዓ.ም በየትምህርት ቤቱ በመዝጊያ ስነስርዓት የትምህርት ማስረጃ በመስጠት እንደሚጠናቀቅ ተገልጿል ፡፡