በአዲስ አበባ የዘማች ቤተሰቦችን ሰብል ለሚሰበስቡ 30ሺ መምህራንና ተማሪዎች ሽኝት እየተደረገ ነው

 

******

የዘማች ቤተሰቦችን ሰብል ለመሰብሰብ ለሚሰማሩ ከአዲስ አበባ ከተማ የተለያዩ ትምህርት ቤቶች ለተውጣጡ 30ሺ መምህራንና፣ ተማሪዎች፣ የትምህርት ባለሙያዎች እና አመራሮች የአዲስአበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በተገኙበት አሸኛኘት እተደረገ ነው፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ከህዳር 27 እስከ ታህሳስ 3 ቀን 2014 ዓ.ም ዝግ ሆነው የዘማች አርሶ አደሮች ሰብል እንዲሰበሰብ ውሳኔ ማሳለፉ ይታወሳል፡፡የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ይህን ውሳኔ ተከትሎ "ዘመቻ በትምህርት ልማት ግንባር" በሚል መሪ ቃል የዘማች ቤተሰቦችን ሰብል ለመሰብሰብ የትምህርት ማኅበረሰብ አባላትን ወደ ተለያዩ አካባቢዎች እያሰማራ ነው።በአበበ ቢቂላ ስታዲየም እየተካሄደ በሚገኘው የሽኝት መርሃ ግብር ላይ የተገኙ ተማሪዎች ምዕራባውያን በኢትዮጵያ ላይ እያደረጉት ያለውን ጫናና ጣልቃ ገብነት የሚቃወም መፈክር እያሰሙ ይገኛሉ።

Share this Post