በኢትዮጵያ ሰላምን በማስፈን እና የሀገርን ህልውና በማስጠበቅ ረገድ የሀይማኖት ተቋማት ሚናቸውን በአግባቡ ሊወጡ ይገባል ተባለ፡፡

"ሀይማኖታዊ የጋራ እሴቶች ለሰላም እና ለሀገራዊ አንድነት"በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ አዘጋጅነት ከሁሉም የእምነት ተቋማት የተውጣጡ የሀይማኖት አባቶች በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት በማካሄድ ላይ ይገኛሉ፡፡

የእምነት ተቋማት ፣መሪዎች፣ አባቶች እና መምህራን ትውልድን በመቅረጽ፣ የህብረተሰብ ትስስር በማጠናከር ፣ሀገራዊ አንድነትንና ህዝብን ከህዝብ የሚከፋፍሉ እኩይ ተግባራትን እንዲጸየፉ ለተከታዮቻቸው ሊያስተምሩ እንደሚገባ በውይይት መድረኩ ተገልጿል፡፡

የሀይማኖት ተቋማት ሀገሪቱ አሁን ያለችበትን አስቸጋሪ ሁኔታ እንድትሻገር እና ሰላም እንዲሰፍን ተገቢውን ስራ በመስራት የሀገርን ህልውና በማስጠበቅ ረገድም ሚናቸውን በአግባቡ ሊወጡ ይገባል ተብሏል፡፡

ወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይን አስመልክቶ ከትላንት ጀምሮ በመካሄድ ላይ ባለው የውይይት መድረክ ለሀገርና ለህዝብ ህልውና የሃይማኖት ተቋማት ሚና ፣ፐብሊክ ድፕሎማሲ የዜጎች ተሳትፎና አስተዋጽኦ እና ሀሰተኛ መረጃዎች ስርጭትና አሉታዊ ተጽእኖ በሚሉ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ በተለያዩ ክፍለከተሞች ምክክር እየተካሄደ ነው፡፡

 

Share this Post