በወራሪው ህወሓት ላይ እየተገኘ ያለው ድል የኢትዮጵያዊነት ስነ ልቦና ከድል ጋር ብቻ የተሰፋ መሆኑን ማሳያ ነው " ምሁራን

 

በወራሪው እና ሽብርተኛው ህወሓት ላይ እስካሁን እየተገኘ ያለው አመርቂ ድል የኢትዮጵያዊነት ስነ ልቦና ከድል ጋር ብቻ የተሰፋ መሆኑን ማሳያ ነው ብለዋል ምሁራን።

ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ያደረጉት የጂማ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ መምህር እና ተመራማሪ ረዳት ፕሮፌሰር ተመስገን ለሜሳ እና የባህርዳር ዩኒቨርሲቲው የፖለቲካ ሳይንስ እና ዓለም አቀፍ ትምህርት ክፍል መምህሩ ዶክተር በእውቀቱ ድረስ በጥቂት ቀናት በሽብርተኛው ቡድን ላይ ያገኘነው ወታደራዊ የበላይነት የመተባበር እና የአንድነታችን ማሳያ ነው ብለዋል።

ጦርነቱ ሽብርተኛው እና ወራሪው ቡድን ከእነ እሳቤው ሊወገድ በሚችልበት እና ዳግም የኢትዮጵያ ሰላም ጸር ወደማይሆንበት እስከሚሸጋገር ድረስ የሚቀጥል መሆኑንም አስምረውበታል።

ከዚህ አንጻርም ይህን የመጨረሻ ግብ ታሳቢ በማድረግ በጀመርነው ጎዳና እና ትኩሳት መትመም አለብንም ነው ያሉት።

የህዝቡ ድጋፍ እና አካባቢውን በንቃት መጠበቅም ሳይሸራረፍ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል ምሁራኑ።

ዳያስፖራውም በአግባቡ ገንዘብ በመላክ፣ በተለያዩ አማራጮች አገርን በገንዘብ በመደገፍ እና የተለያዩ መድረኮችን እየፈጠሩ የሽብርተኛውን ቡድን ጭካኔ ለዓለም ማጋለጣቸውን እንዲቀጥሉም ጠይቀዋል።

በአገር ውስጥ ያሉ ዜጎችም በግንባር መዝመት የሚችሉት አሁን ከጸጥታ ሀይሉ ጎን እንዲሰለፉም ጥሪ አቅርበዋል።

ከዚህ ባለፈም ሌሎች በደጀንነት አካባቢን በንቃት መጠበቅ እንዳለባቸውም አጽንኦት ሰጥተዋል።

Share this Post