በገና ኤግዚቢሽንና ባዛር ከ400 በላይ የውጭና የአገር ውስጥ ድርጅቶች ይሳተፋሉ

 

የፊታችን ቅዳሜ በሚከፈተው የገና ኢግዚቢሽንና ባዛር ከ400 በላይ የውጭና የአገር ውስጥ ድርጅቶች ለመሳተፍ መመዝገባቸውን የኤግዚቢሽን ማዕከልና የገበያ ልማት ድርጅት አስታወቀ።የድርጅቱ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ጥላሁንታደሰ፤ኢግዚቢሽንና ባዛሩን በማስመልከት መግለጫ ሰጥተዋል።

የፊታችን ቅዳሜ ታህሳስ 9 ቀን 2014 ዓ.ም በኤግዚቢሽን ማእከል በሚከፈተው ባዛር ከ400 በላይ የአገር ውስጥና የውጭ ድርጅቶች የሚሳተፉ መሆኑን ገልጸዋል።ኢግዚቢሽንና ባዛሩ ዋነኛ ዓላማ ምርቶችን ማስተዋወቅ፣ ገዥና ሸማቹን ማገናኘትና እየተስተዋለ ያለውን የዋጋ ንረት ማረጋጋት መሆኑን አብራርተዋል።ቀደም ብሎ የቦታ ክራይና የመግቢያ ዋጋ ላይ ቅሬታ ይቀርብበት የነበረው ኢግዚቢሽነና ባዛር ይህንን ቅሬታ ሊፈታ በሚችል መልኩ ተዘጋጅቷል ሲሉም አቶ ጥላሁን ገልጸዋል።ኤግዚቢሽንና ባዛር አገራዊ ፋይዳ ባለው መልኩ እንዲካሄድ በማድረግ የአዲስ አበባን ሰላማዊ እንቅስቃሴ ለማስተዋወቅ ይጠቅማል ብለዋል።ለኤግዚቢሽንና ባዛሩ ከተሸጠው 2 በመቶውን ለአገር መከላከያ ሰራዊትና ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ የማዋል እቅድ መያዙንም አስረድተዋል።

ድርጅቱ ከዚህ ቀደም ከሰራተኛው የወር ደሞዝ ከ8 ሚሊዮን ብር በላይ ተመሳሳይ ድጋፍ ማድረጉን አስታውሰዋል።

Share this Post