በ217 ሚሊዮን ብር ወጪ በቀዳማዊት ጽ/ቤት አማካኝነት በአዲስ አበባ ከተማ የተገነባው የዳቦ ፋብሪካ ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት ተደረገ።

 

ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው የዳቦ ፋብሪካውን ቁልፍ ለአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዛሬው ዕለት አስረክበዋል ።የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በዳቦ ፋብሪካው ርክክብ ወቅት እንደገለጹት በከተማዋ የኑሮ ውድነትን መንስኤ የአቅርቦት እና ፍላጎት አለመጠጣም ችግር ነው ብለዋል።ኢትዮጵያን የመለወጥ እና የማበልጸግ ጊዜ ላይ እንገኛለን ያሉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ በከተማችን የኑሮ ውድነቱን ለማቃለልም የቀዳማዊ እመቤት ጽ/ቤት የደሀውን ማህበረብ ተጠቃሚ ዳቦ ፋብሪካ ከፍተው በማስረከባቸው በከተማዋ ነዋሪዎች ስም አመስግነዋል።

ፋብሪካው ከዳቦ ማምረት ባለፈ ለእናቶች የስራ እድል የሚፈጥር መሆኑን ገልጸው የገለፁት ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለእናቶች የመሸጫ ቦታ በማዘጋጀት ዳቦው በቀላሉ የሚሰራጭበትን ሁኔታ እንደሚመቻች ይደረግላቸዋል ብለዋል።ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በበኩላቸው ይሄ የዳቦ ፋብሪካ የስንዴ አቅርቦት ችግር እንዳይገጥመው ከክልል የስንዴ አምራች ገበሬዎች በቀጥታ የሚያገኝበት ሁኔታ ይመቻቻል ብለዋል።ይህ ፋብሪካ ተገንብቶ በዚህ ደረጃ እውን እንዲሆን የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት በሙሉ ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ምስጋናቸውን አቅርበዋል ።በቀዳማዊት እመቤት ፅ/ቤት 217 ሚሊየን ብር በአዲስ አበባ ከተማ ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ በ6ሺህ ካሬ ሜትር ላይ የተገነባው ዳቦ ፋብሪካው በቀን 1 ሚሊዮን ዳቦ በማምረት አቅም ያለው ሲሆን ለ450 ዜጎች የስራ እድል የሚፈጥር ይሆናል።

Share this Post