ነዋሪዎች የአካባቢያቸውን ሰላምና ደህንነት በመጠበቅ ረገድ ከፀጥታ ሃይሉ ጋር የጀመሩትን ተግባር አጠናክረው እንዲቀጥሉ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ጥሪ አቀረቡ። ህገወጥ የጦር መሳሪ...

ነዋሪዎች የአካባቢያቸውን ሰላምና ደህንነት በመጠበቅ ረገድ ከፀጥታ ሃይሉ ጋር የጀመሩትን ተግባር አጠናክረው እንዲቀጥሉ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ጥሪ አቀረቡ። ህገወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር እና መሰል ድርጊቶች በከተማችን ነዋሪዎች ተባባሪነትና በፀጥታ ሃይሉ ጥብቅ ክትትል ለታለመላቸው የጥፋት ድግስ ሳይውሉ እየከሸፉ ነው ያሉት ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በዛሬው ዕለትም በተሽከርካሪ ተጭነው ሲዘዋወሩ የነበሩት 6 ሺህ ጥይቶችና 98 ሽጉጦች በቁጥጥር ስር መዋሉን ተናግረዋል ። ዛሬ ማምሻውን በቦሌ ክፍለ ከተማ ልዩ ስሙ ሚሊኒየም ፓርክ ተብሎ በሚጠራዉ ስፍራ 58 ቱርክ ሰራሽ ሽጉጦች፤ 1ሺህ 988 የብሬን፣ 1ሺህ 576 የሽጉጥ እና 154 የሌሎች መሳሪያዎች ጥይቶች በአዲስ አበባ ፖሊስ፣ በብሄራዊ መረጃ ደህንነት ፀጥታ ሃይል በተደረገ ...ክትትል በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ገልጸዋል ። የመኪና ባለንብረቶችና አከራዮች ተሽከርካሪያቸውን በምን አይነት ስምሪት ላይ እንዳሉ መከታተል ይገባቹኃልም ሲሉ ምክትል ከንቲባዋ በመልዕክታቸው አሳስበዋል ።

Share this Post