አመራሩ የህብረተሰቡን ጥያቄ ለመመለስ በሚያስችል መልኩ የቀጣይ 100 ቀናት ዕቅድ በማውጣት በፍጥነት ወደ ተግባር እንዲገባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ አሳሰቡ።

 

"ለአዲስ ምዕራፍ ተልዕኮ ዝግጁ ነን!" በሚል መሪ ቃል ከከተማ እስከ ወረዳ አዲስ ለተመደቡ አመራሮች የስራ ስምሪት እና የትኩረት አቅጣጫ የውይይት መድረክ ተጠናቋል ።የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በውይይቱ ማጠቃለያ እንዳስታወቁት አመራሩ የተሰጠውን ህዝብን የማገልገል ኃላፊነት በአግባቡ መወጣት ይኖርበታል ብለዋል፡፡በየደረጃው ያለ አመራርም በየተቋሙ የህብረተሰቡን ጥያቄ መመለስ በሚያስችል መልኩ የቀጣይ 100 ቀናት ዕቅድ በማውጣት በፍጥነት ወደ ተግባር መግባት እንዳለበትም ከንቲባ አዳነች አቤቤ አሳስበዋል ።የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የመንግስት ዋና ተጠሪ አቶ መለሰ አለሙ በበኩላቸው ሀገራዊ ለውጡ ለሀገር ግንባታ እንዲውል ለማድረግ አመራሩ የለውጡን ሳንካዎች ጠንቅቆ ማወቅ እንደሚገባው ጠቁመዋል፡፡

ብልጽግና ፓርቲ በምርጫ ወቅት ያስተዋወቀውን ማኒፌስቶ በተግባር በመተርጎም ቃልን ማክበር እንደሚገባ አቶ መለሰ በውይይቱ አስረድተዋል ።

ኢትዮጵያን ከአፍራሾች ለመታደግና ዴሞክራሲን ለመትከል ለተጫወቱት ላቅ ያለ ሚና ዜጎችን መካስም የአመራሩ የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ መሆኑን እንዳለበት አቶ መለሰ ዓለሙ ገልፀዋል።የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የስራ ኢንተርፕራይዝ እና ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ በበኩላቸው አንዳንዶቹ የህዝብ ጥያቄዎች አመራሩ ተጨማሪ አቅም ሳያስፈልገው በቅንነት የሚመለሱ ስለሆኑ አመራሩ በቁርጠኝነትና በስነምግባር ሊረባረብ እንደሚገባ አመልክተዋል።

Share this Post