በዛሬው እለት ምስረታውን በይፋ ያካሄደው የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የካቢኔ አባላትን ሹመት በማጽደቅ ተጠናቋል ።
ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ የካቢኔ አባላትን ለምክር ቤቱ ያቀረቡ ሲሆን ምክር ቤቱም በቀረቡ እጩዎች አስተያየት በመስጠት አጽድቋል ።
የቀረቡት እጩዎች የረዥም ጊዜ የስራ ልምድ፣የትምህርት ዝግጅት እና በመሩት ተቋማት ውጤታማ አፈጻጸም የነበራቸው መሆኑን ተገልጿል ።
በተጨማሪም ከተለያዩ ተፎካካሪ ፖለቲካ ፓርዎች የተካተቱበት ካቢኔ እንዲሆን ተደርጓል ።
በዚሁ መሠረት፦
1.ዶ/ር ቀነአ ያደታ የሰላምናጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ
2.ዶ/ር ሂሩት ካሳው የባህል፤ኪነጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ
3.ወ/ሮ ጽዋዬ ሙሉነህ የፍትህ ቢሮ ኃላፊ
4.አቶ ጀማል አሊዬ የመሬት ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ
5.አቶ ዳዊት የሺጥላ የትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ
6.ኢ/ር ሀያልነሽ ሀብተማሪያም የዲዛይን እና ግንባታ ቢሮ ኃላፊ
7.ዶ/ር ሙሉቀን ሀብቱ የቴክኒክ ሙያ ፣ስልጠና እና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ ኃላፊ
8.ዶክተር ዮሃንስ ጫላ የጤና ቢሮ ኃላፊ
9.አቶ አደምኑር ዋበላ የንግድ ቢሮ ኃላፊ
10.አቶ ዘላለም ሙላቱ የትምህርት ቢሮ ኃላፊ
11.ዶ/ር ሀና የሺንጉስ የሴቶች ፣ህጻናት እና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ
12.አቶ ሙሉጌታ ተፈራ የገቢዎች ቢሮ ኃላፊ
13.አቶ አብረሃም ታደሰ የወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ
14.አቶ ዮናስ ዘውዴ የኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ
15.ወ/ሮ ጽጌሬዳ ወርቁ የከተማ ውበት እና አረንጓዴ ልማት ቢሮ ኃላፊ
16.ዶ/ር ዳዲ ወዳጆ የፕላን ኮሚሽን ኮሚሽነር
17.አቶ ግርማ ሰይፉ የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር
18.አቶ ዩሱፍ ኢብራሂም ሽፈራው የመንግስት ንብረት አስተዳደር ባለስልጣን በመሆን ተሹመዋል።