ኢትዮጵያን የማዳን የገቢ ማሰባሰቢያ መርሐግብር ከ1ቢሊዮን 540 ሚሊዮን ብር በላይ ተሰበሰበ።

 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሀገር መከላከያን እና አሸባሪው የህውሃት ቡድን በከፈተው ጦርነት የተፈናቀሉ ዜጎችን ለማቋቋም ማምሻውን በተካሄደው የገቢ ማሰባሰባ መርሐግብር 1 ቢሊዮን 540 ሚሊዮን 732 ሺህ ብር መሰብሰብ ተችሏል።በሸራተን አዲስ ሆቴል በተካሄደው የገቢ ማሰባሰብ መርሐግብር ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ፣የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ፣ የሀገር መከላከያ ሰራዊት የሰራዊት ግንባታ ስራዎች አስተባባሪ ሌተናል ጀነራል ባጫ ደበሌ፣ የኢፌዴሪ ሀገር መከላከያ ሚንስትር ዶ/ር አብረሃም በላይ፣ የሀይማኖት አባቶች እና ባለሃብቶች ተሳትፈዋል ።

በአንድ ጀምበር ከተሰበሰበው ከ1.ቢሊዮን 540 ሚሊዮን 732 ሺህ ብር የኢትዮጵያ ባንኮች ማህበር 1 ቢሊዮን 23 ሚሊዮን 581ሺህ ብር ድጋፍ ያደረገ ሲሆን ቀሪውን በከተማዋ የሚገኙ ባለሀብቶች ፣ የተለያዩ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት እንዲሁም ግለሰቦች ናቸው

Share this Post