11
Dec
2021
ኢትዮጵያዊው ለገሰ ሞገስ በወታደራዊ መኮንንነት ባሳየዉ የላቀ አፈፃፀም የመጀመሪያው የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ ሆነ
ኢትዮጵያዊው ለገሰ ሞገስ በወታደራዊ መኮንንነት በአለም ዝነኛ በሆነው የሮያል ሳንድረስት የጦር አካዳሚ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ የወርቅ ሜዳሊያ ተሸላሚ ሆነ።
ከተለያዩ አገሮች የመከላከያ ተቋማት ለከፍተኛ ወታደራዊ መኮንንነት እየተቀበለ የሚያሰለጥነው ዝነኛው የሮያል ሳንድረስት የጦር አካዳሚ ባለፈው ዓመት ከ38 አገሮች ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖችን መልምሎ ወታደራዊ ሥልጠና ሲሰጥ ነበር፡፡
በዚህም ኢትዮጵያዊው ለገሰ ሞገስ ከሁሉም አገሮች ሰልጣኞች በሁሉም ወታደራዊ ጥበብ መስኮች በጦር መኮንንነት በጦር ንድፈ ሀሳብ እና የጦር ተግባራዊ ሳይንስን በተመለከተ ባሳየው ጥበብና እውቀት ብልጫ በማሳየቱ የወርቅ ሜዳሊያ እንደተሸለመ በምረቃው ስነ ስርአት ላይ ተገልጿል።
ለገሰ ሞገስ ዘመኑ የደረሰበትን ወታደራዊ ሳይንስና ጥበብ በተሟላ መልኩ በመፈጸሙ የጦር አካዳሚው የሚሰጠውን ከፍተኛ ሜዳሊያ ከመላው ሀገሮች የተወከሉ ወታደራዊ የጦር መኮንኖች የእንግሊዝ ልኡላዊያን ቤተሰቦች የተለያዩ ሀገሮች አምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች እንዲሁም የሮያል ሳንድረስት የጦር አካዳሚ አመራሮች በተገኙበት የእንግሊዝ ልእልት እጅ የወርቅ ሜዳሊያውን ተቀብሏል።