ኢትዮጵያዊ ጨዋነትና አብሮነት እሴቶችን በማዳበር ይህን ወሳኝና አስቸጋሪ ጊዜ በጋራ ለማለፍ ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ጥሪ አቀረቡ።

ምክትል ከንቲባ / አዳነች አቤቤ በከተማዋ በመኖሪያ ቤት ኪራይ ላይ የሚታየውን የኪራይ ዋጋ ጭማሪን ለመከላከል የወጣውን ደንብ አስመልክቶ መልዕክት አስተላልፈዋል

የወቅቱን ሁኔታ ያላገናዘበ የቤት ኪራይ ጭማሪ የነዋሪውን ሕይወት በእጅጉ እየፈተነው እንደሚገኝ ይታወቃል ያሉት ምክትል ከንቲባዋ ይህን በመኖሪያ ቤት ኪራይ ላይ የሚታይ ጭማሪ ለመከላከል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ 18/12/13 . ጀምሮ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ዋጋ መጨመርም ሆነ ተከራይን ከቤት ማስወጣት 90 ቀናት መከልከሉን ገልጸዋል

የክልከላዉ ቀን እንደሁኔታው ሊራዘም እንደሚችል የገለፁት ምክትል ከንቲባ / አዳነች አቤቤ ደንቡን ተላልፎ የኪራይ ጭማሪ ያደረገ አከራይ በደንቡ መሰረት ተጠያቂ እንደሚሆን አሳስበዋል ምንም እንኳን ይህ ደንብ የወጣው ዜጎችን ከአላስፈላጊ ጫና ለመከላከልና ጥፋተኞችን ተጠያቂ ለማድረግ ቢሆንም ህዝባችን ችግሮችን በመተሳሰብና በመደጋገፍ ኢትዮጵያዊ የጨዋነትና የአብሮነት እሴቶቹን በማዳበር ይህን ወሳኝና አስቸጋሪ ጊዜ በጋራ ማለፍን ማዕከል በማድረግ ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣ ጥሪዬን አቀርባለሁ ብለዋል።

Share this Post