ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!!

የአዲስአበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ የትስስር ገፃቸዉ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ዐህመድ በድል መመለሳቸዉን አስመልክቶ መልዕክት አስተላልፈዋል " ጀግናው የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትርና ዶክተር አብይ ዐህመድ እንኳን በድል አድራጊነት ተመለሱ!!"ያሉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ

"ምንጊዜም ለኢትዮጵያ የሚመኙት ፤ ሌትና ቀን የሚለፉለት፤ የሚታገሉለት አይቀሬው የኢትዮጵያ ብልፅግና በአመራር ዘመንዎ እዉን እንዲሆን በራሴና በአዲስአበባ ከተማ አስተዳደርና ነዋሪዎች ስም ከልቤ እየተመኘሁ እንደ ትላንቱ ፣ ዛሬም ፣ምንጊዜም መላው የአዲስአበባ ከተማ ነዋሪ በታላቅ የአገር ፍቅር ስሜት በየትኛውም ግምባር ከጎንዎ እንደሆነ ዳግም እናረጋግጣለን !! ብለዋል።

ኢትዮጵያ በልጆቿ ጥረት ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኑር!!

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ !!"

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ሕዳር 29፤2014 ዓ.ም

Share this Post