10
Jan
2022
እምነት፣ ብሔርና ቋንቋ ሳይገድበን ሀገራችንን ከጥፋት ኃይሎች ታድገናል ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ተናገሩ፡፡ከንቲባዋ ይህን ያሉት በዘጸዓት አፖስቶሊክ ሪፎሜሸን ቤተክርስቲያን ባዘጋጀው ለተፈናቀሉ ወገኖች ገቢ ለማሰባሰብ በተካሄደ መርሃ ግብር ነው፡፡ጠላቶቻችን ኢትዮጵያ እንድትፈርስ ቢያሴሩም ያለምንም የእምነት፣ ብሔርና ቋንቋ ሳይገድበን ሀገራችንን ከጥፋት ኃይሎች ታድገናል ነው ያሉት፡፡
ሁላችንም ጠላት ሀገራችንን ሊያፈረስ ሲነሳ በምንም አልተለያየንም ፤ አሁንም ኢትዮጵያ የጋራችን በመሆኗ በመተባበር ለተፈናቀሉ ወገኖች ልንደርስ ይገባል ብለዋል፡፡ለተፈናቀሉ ወገኖቻንን በመድረስ ደግሞ የእምነት ተቋማት ሚናቸውን መወጣት እንደሚገባቸው ከንቲባዋ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በዘጸዓት አፖስቶሊክ ሪፎሜሸን ቤተክርስቲያን በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ በተዘጋጀው መድረክ ለተፈናቀሉ ወገኖች የሚሆን ገቢ ተሰባስቧል፡፡በመርሃ ግብሩ ላይ የዘጸዓት አፖስቶሊክ ሪፎሜሸን ቤተክርስቲያን ዋና መጋቢ ሀዋሪያው ዮሐንስ ግርማ፣ የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት ፕሬዝዳንት መጋቢ ጻድቁ አብዶ ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት ስራ ኃላፊዎች፣ የእስልምና መምህሩ ኡስታዝ አቡበከር አሕመድ ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸውን እንግዶችና የእምነቱ ተከታዮች ታድመዋል፡፡