እኔ የከተማዬ የሠላም ዘብ ነኝ

እኔ የከተማዬ የሠላም ዘብ ነኝ "በሚል በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ ክፍለ ከተሞች የአካባቢን ሰላም እና ጸጥታ ለማሰጠበቅ ስልጠና የወሰዱ በጎፈቃደኞች ወደ ስራ ገቡ፡፡

በየካ ፣በለሚ ኩራ፣ ኮልፌ ቀራኒዮ ፣ በቂርቆስ እና በልደታ ክፍለ ከተሞች በወንጀል መከላከል፣በህዝብ ደህንነት እና ሰላም እንዲሁም በሰላም እሴቶች ዙሪያ ስልጠናቸውን የተከታተሉ በሺዎች የሚቆጠሩ በጎፈቃደኞች ተመርቀው ወደ ስራ ተሰማርተዋል፡፡

በቀሪ ክፍለ ከተሞችም የከተማዋን ሰላምና ደሕንነት ለመጠበቅ ስልጠና በመውሰድ ላይ ሲሆን በጠቅላላው ከ27 ሺህ በላይ በጎፈቃደኞች ባሉበት ብሎክ እና ወረዳ የአካባቢያቸውን ሰላም ለመጠበቅ በዝግጅት ላይ ይገኛሉ፡፡

Share this Post