ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለመውሊድ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ።

 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በነገው ዕለት ለሚከበረው ለ1 ሺህ 496 ኛዉ የመውሊድ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል ።

በአሉን ስናከብር እንደከዚህ ቀደሙ የተቸገሩ ወገኖችን በመርዳት ፣ ያለው ለሌሎች በማካፈል፣ የታረዙትን በማልበስ ፣የወደቁትን በማንሳት ፣ የታመሙትን በመዘየር እና ለምድራችን ሰላም ዱአ በማድረግ እንዲሆን እመኛለሁ ብለዋል ከንቲባ አዳነች አቤቤ

Share this Post