ከንቲባ አዳነች አቤቤ በቢሾፍቱ የመከላከያ ሰራዊት ኮምፕሬሲቭ ስፔሻላይድ ሆስፒታል በመገኘት የሰራዊት አባላትን ጎበኙ።

 

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በቢሾፍቱ የመከላከያ ኮምፕሬሲቭ ስፔሻላይድ ሆስፒታል በመገኘት በህልውና ዘመቻው ጉዳት የደረሰባቸውን የመከላከያ ሰራዊት አባላት በመጎብኘት 15 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የህክምና ቁሳቁስ እና የተለያዩ አልባሳት ድጋፍ አድርገዋል በኢትዮጵያ ላይ የመጣውን አደጋ ለመመከት የተዋደቁ እና የጀግንነት ተግባር ፈጽመው ጉዳት የደረሰባቸውን የሰራዊታችንን አባላት ማበረታታት እንደሚገባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገልጸዋል

የመከላከያ ሰራዊት ኮምፕሬሲቭ ስፔሻላይድ ሆስፒታል በሙሉ አቅሙ አገልግሎት እንዲሰጥ ከህክምና ቁሳቁስ ጀምሮ አስፈላጊው ሁሉ እንዲሟለለት የከተማ አስተዳደሩ ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል።የቢሾፍቱ መከላከያ ሰራዊት ኮምፕሬሲቭ ስፔሻላይድ ሆስፒታል አዛዥ /ጀነራል ተገኝ ለታ የከተማ አስተዳደር ላደረገው የህክምናና የአልባሳት ድጋፍ በሰራዊቱ ስም አመስግነዋል።

ዛሬ ከተደረጉት የህክምና ቁሳቁሶች መካከል 400 ዘመናዊ አስተኝቶ ማከሚያ አልጋዎች በአዲስ አበባ ከተማ ጤና ቢሮ አማካኝነት የተደረገ ሲሆን 2ሺህ ሙሉ ቱታዎች እና ልዩ ልዩ አልባሳት ከአዲስ አበባ ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ የተደረጉ በጠቅላላው 15 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመቱ ናቸው።

Share this Post