ከንቲባ አዳነች አቤቤ በትናትናው እለት ከማለዳ ጀምሮ በመስቀል አደባባይ በተካሄደው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ለተሳተፉ ነዋሪዎች እና የጸጥታ አካላት ምስጋና አቀረቡ።

 

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ / አዳነች አቤቤ ከሌሊት አንስቶ በታሪካዊዉ የመስቀል አደባባይ በመገኘት አገር መሆን ከምንም በላይ እንደሆነ ያስመሰከራችሁ ምስጋዬ ይድረሳችሁ ብለዋል።ለጀግናዉ የመከላከያ ሀይላችን በድጋሚ ደጀንነታችሁን ያረጋገጣችሁ መላዉ የከተማችን ነዋሪዎች፣ የሀይማኖት አባቶች፣ ወጣቶችና ሴቶች፣ የተፎካካሪ ፓርቲ አመራሮችና አባላት እንዲሁም ሰላማዊ ሰልፉ በተሳካ ሁኔታ በሰላም እንዲጠናቀቅ አስተዋጽኦ ላበረከቱ የፀጥታ ሀይሎች በሙሉ ለኢትዮጵያ ጥሪ በአንድነትና በፍፁም ኢትዮጵያዊነት ለሰጣችሁት ከፍተኛ የአገር ፍቅርና ወኔ የታየበት ምላሽ እጅጉን የከበረ ምስጋናዬን አቀርባለሁ " ብለዋል።

Share this Post