25
Oct
2021
የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በትራንስፖርት ቢሮ እና ተጠሪ ተቋማት አማካኝነት በክረምት ወራት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት በጉለሌ ከተማ ክፍለ ከተማ የታደሱ ቤቶችን በዛሬው ዕለት አስረክበዋል፡፡
ባለፉት ወራት በክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት መርሀግብር ከሁለት ሺህ በላይ ቤቶች እድሳት በማድረግ፣ወላጅ አልባ ህጻናትን በማሳደግ ፣ለመከላካያ ሰራዊት ድጋፍ በማሰባሰብ እና በልዩ ልዩ ተግባራት መሰራታቸውን ከንቲባ አዳነች አቤቤ በርክክቡ ወቅት ተናግረዋል፡፡
መረዳዳት እና መተጋገዝ የኢትዮጵያዊያን ባህል ነው ያሉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ በክረምት በጎ ፈቃድ መርሃግብርም የመንግሥትን ጥሪ ተቀብለው በተለያዩ የበጎ አድራጎት ሥራ የተሳተፉ ተቋማት እና ግለሰቦች እንዲሁም ወጣቶች ምስጋና ይገባቸዋል ብለዋል።
በዛሬው ዕለት ቤታቸው ለታደሰላቸው ወ/ሮ እቴነሽም በየወሩ የአንድ ሺህ አስቤዛ ለመስጠት ከንቲባዋ ቃል የገቡ ሲሆን ሌሎች በጎ ፈቃደኛ ግለሰቦችም በችግር ውስጥ ለሚገኙ ዜጎችን ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡